አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያ የ90.6 ሚሊዮን ብር አክሲዮን በመግዛት መስራች ባለቤት ሆነ

Home / Announcements / አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያ የ90.6 ሚሊዮን ብር አክሲዮን በመግዛት መስራች ባለቤት ሆነ

የኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ጠንካራ ሆኖ እንዲቋቋም እና ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ አማራ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ተወያይቶ ባፀደቀው መሠረት ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በመመደብ የ10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ የገዛ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲተመን ብር 90.6 ሚሊዮን መሆኑን መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ለገሀር በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሔደው ጋዜጣዊ መግለጫ የባንኩ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጫንያለው ደምሴ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል፡፡

የአክሲዮን ግዢ ስምምነት ፊርማው የአማራ ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጫንያለው ደምሴ እና የኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማዔል በተገኙበት የተፈጸመ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ አማራ ባንክ ምንጊዜም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለህዝብ ኑሮ መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት ዋነኛ መገለጫው መሆኑን ተገልጿል፡፡

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2024 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved