በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው አማራ ባንክ የሚሰጣቸውን የፋይናንስ አገልግሎቶች ለጎብኝዎች አቀረበ።

Home / Uncategorized / በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው አማራ ባንክ የሚሰጣቸውን የፋይናንስ አገልግሎቶች ለጎብኝዎች አቀረበ።

የአማራ ባንክ የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ እሸቴ የማታ የዲጂታል ባንክ ሽግግርን ለማፋጠን ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም አማራ ባንክ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርብ ዓመታት ዘርፉን የተቀላቀለ የፋይናንስ ተቋም እንደመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው እና ከ1200 በላይ የፋይናንስ ሴክተር ባለድርሻ አካላትን፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን፣ ተቆጣጣሪዎችን እና የሴት የፋይናንስ መሪዎችን ባሰባሰበው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ ተሳታፊ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል። በዚሁ ፎረም ላይ አማራ ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ንግዶችን ለመደገፍ እና በሀገራችን ያሉ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማብቃት ታስበው የተዘጋጁ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ መሆኑን የሚያሳዩ ስራዎችን ለእይታ አቅርቧል።
የአማራ ባንክ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ የሆኑት አቶ እሸቴ የማታ እንዳሉት፥ “በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ በመሳተፋችንና የፋይናንስ ዘርፉን ምህዳር የወደፊት ዕጣ በሚወስኑ ወሳኝ ዉይይቶች ላይ አስተዋፅዖ በማድረጋችን እጅግ ደስተኞች ነን። አማራ ባንክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማስፋት፣ ስራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት እና በመላ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን በቁርጠኝነት እየሰራ ያለ ባንክ ነው። የፋይናንስ ተደራሽነትንና ዘላቂ ልማትን ለማሳደግ ትልቅ የፈጠራና ትብብር እድል እንዳለ እናምናለን፤ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ እንደ ባለድርሻ አካል ያለብን ኃላፊነት እንደሆነ እናምናለን።”
በተጨማሪም አማራ ባንክ የሚሰጣቸውን የባንክ አገልግሎቶች በፋይናንስ ጉባኤ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች ከማቅረብ ባሻገር፣ አሁን ያሉ አገልግሎቶችን ይበልጥ ሊያሳድጉና ደንበኞቹን በተሻለ ሁኔታ ሊያገለግሉ የሚችሉ በፈጠራ የታገዙ አገልግሎቶችን ለመፈለግ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር ለመስራት በንቃት እንደሚሳተፍ ተገልጿል።
የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዘጋጅነት ግንቦት 7 እና 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

 

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2024 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon