አማራ ባንክ የ1446ኛውን የረመዷን ጾም እና የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አደረገ!

Home / Announcements / አማራ ባንክ የ1446ኛውን የረመዷን ጾም እና የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አደረገ!

(ሀሙስ መጋቢት 18 ቀን 2017) አማራ ባንክ የ1446ኛውን የረመዷን ፆም እና የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አደረገ! በመርሃ-ግብሩ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በተለያዩ አካባቢዎች በመገኘት ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የአማራ ባንክ መርሃባ – ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ተወካይ ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት ተስፋዬ በድጋፍ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ባንኩ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ የሸሪአ መርህን መሠረት ያደረገ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት መስጠቱ በርካታ የአገራችንን ህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ ያስችላል ያሉት ወ/ሮ መሰረት፤ መርሃባ የአማራ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች እንዲሁም ለአገልግሎቱ በተለዩ 14 ቅርንጫፎች እየሰጠ በመሆኑ ገልጸዋል።

አገልግሎቱ ካለው ፍላጎት አንጻር ሲታይ አሁንም ተካታች ያልሆነ የህብረተሰብ ክፍል ብዙ በመሆኑ፤ ህብረሰተቡ የሚፈልገውን አማራጭ በማቅረብ ማገልገል እንደሚገባና አማራ ባንክ የዋዲዓህ፣ አማና፣ ቀርድ እና የሙደረባህ ኢንቨስትመንት፣ እና ሌሎችንም አገልግሎቶች እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የመርሃባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ጋብዘዋል፡፡

አማራ ባንክ ከተመሰረተ ካለፉት ሶስት ዓመታት ጀምሮ የዒድ አልፈጥር በዓልን ጨምሮ የተለያዩ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች ለአቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ እያካሄደ መሆኑም ተገልጿል፡፡
አማራ ባንክ መጪው የዒድ አልፊጥር በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆን ይመኛል!

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2024 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved

wpChatIcon
wpChatIcon