አማራ ባንክ ቅዳሜ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም የባለአክሲዮኖች የአክሲዮን ምስክር ወረቀት መስጫ መርሃ ግብር በይፋ ያስጀመረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጋሻው ደበበና ሌሎች የቦርድ አባላት፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌውና የስራ አስፈጻሚ አባላት በተገኙበት ይፋዊ የአክሲዮን ባለድርሻነታቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት የማስረከብ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጋሻው ደበበ ለገዙት አክሲዮን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት መጀመሩን አብስረዋል፡፡
የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው ለሁሉም ባለአክሲዮኖች የባለድርሻ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀታቸውን በአጭር ጊዜ ለማስረከብ በቂ ዝግጅት መደረጉንና ባለአክሲዮኖች በዋና መስሪያ ቤት እና በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት መውሰድ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡