አማራ ባንክ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በዱባይ ለ10ኛ ጊዜ እየተከበረ ባለው በዱባይና በሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ቀን ላይ በመገኘት ከማህበረሰቡ ጋር አብሮ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ፡፡
በውይይቱ ላይ በዱባይ የኢትዮጵያ አምባሳደር አክሊሉ ከበደ፣ ዲፕሎማቶች፣ በዱባይና በሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ቦርድ ሰብሳቢ እና ማኔጅመንት አካላት፣ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት፣ ምሁራን፣ አርቲስቶች እንዲሁም ልዩ ልዩ ተቋማት ተገኝተዋል::