(የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም) አማራ ባንክ በፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ዙሪያ እያካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል በማቀድ ከአለም አቀፍ የሥርዓት ዲዛይንና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት (ጉዛም ቴክኖሎጂ) ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው እለት ተፈራረመ።
አማራ ባንክ ከጉዛም ጋር በቴክኖሎጂ መፍትሄዎች ዙሪያ ሰተራቴጂክ አጋርነት በመመስረት ራዕዩን እውን የሚደርግባቸውን ስራዎች ለመስራት መግባባት ላይ ደርሷል፡፡
ጉዛም ቴክኖሎጂ በአማራ ባንክ የሚታዩትን የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ቢዝነስ ክፍተቶችን በመለየት (Gap Analysis) በመስራት የተሻሉ የመፍትሄ አማራጮችን ማስቀመጥ ቀዳሚ ስራው ይሆናል፡፡
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!