ተራፊ አክሲዮኖችን ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን (Diasporas’) ለመሸጥ የወጣ መመሪያ

Home / Agreements / ተራፊ አክሲዮኖችን ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን (Diasporas’) ለመሸጥ የወጣ መመሪያ

በባንካችን መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 5(5.3) መሰረት አማራ ባንክ አ.ማ በንግድ መዝገብ ተመዝግቦ ሥራ ከጀመረበት ሰኔ 11 ቀን 2014ዓ.ም ጀምሮ በሚቆጠር በስድስት ወራት ውስጥ እያንዳንዱ ባለአክሲዮን ከፈረመው አክሲዮን ውስጥ ክፍያ ያልፈጸመበትን ቀሪ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ገቢ ማድረግ ያለበት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ክፍያቸውን ያላጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች በመኖራቸው ይህን ያልተከፈለ ቀሪ አክሲዮን ክፍያን ለነባር ባለአክሲዮኖች በሽያጭ ለማስተላለፍ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡በዚሁ መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነባር ባለአክሲዮኖች ተጨማሪ የአክሲዮን ግዥ ሲፈፅሙ ሊተገበሩ የሚገባቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች እንደሚከተለው በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

1.  በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር 73/2020 መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች የአክሲዮን ግዥውን የሚፈፈጽሙት በአሜሪካን ዶላር፣ በእንግሊዝ ፓውንድ፣ በዩሮ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ባላቸው የሌሎች ሀገራት ገንዘብ ነው፡፡

2.  ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች ክፍያውን መፈጸም የሚችሉት ከሚኖሩበት ሀገር በአማራ ባንክ በኩል ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ካላቸዉ የዲያስፖራ አካውንት /Non-Residence Foreign Currency Account/ በማዘዋወር ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ በውጭ ምንዛሬ የትርፍ ክፍፍል የሚገኝበት ኢንቨስትመንት (ካለ) በውጭ ምንዛሬ ከሚገኝ ገቢ ላይ በባንክ በኩል ወደ አማራ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ በማስተላለፍ ብቻ እና በአዋጅ ቁጥር 270/1994 መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቹህን የሚያረጋግጥ የመታወቂያ ካርድ /ቢጫ ካርድ/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3.   በባንክ ስራ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1159/2011 አንቀጽ 9 መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገዙት አክሲዮን ላይ በትርፍ ክፍፍልም ሆን በዝውውር የሚያገኙትን ገቢ መውሰድ የሚችሉት በኢትዮጵያ ብር ብቻ ይሆናል፡፡(There is no Repatriation Right neither for the dividends nor for the producers of the sale of the shares in any kind of Foreign Currency).

4.  በኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን የጋራ ባለቤትነት የተያዙ ኩባንዎች የሚፈጽሟቸው የአክስዮን ገዥዎች ክፍያቸውን የሚፈጸሙት የኩባንያው ባለድርሻዎች በሚመቻቸው እና በተፈቀዱ የውጭ ምንዛሬ ገንዘቦች ወይም የኢትዮጵያ ብር ይሆናል፡፡

5.  በየትኛውም ዓለም የሚኖሩ ነገር ግን ዜግነታቸውን ያልቀየሩ (ኢትዮጵያዊ የሆኑ)  ገዥዎች የአክስዮን ግዥ ክፍያውን የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ባላቸው ማናቸውም የውጭ ምንዛሬ መክፈል ይችላሉ፡፡

6.  ማንኛውም ተራፊ አክሲዮን ገዥ መግዛት የሚችለው ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ከዚህ በፊት ከነበረው የአክሲዮን ድርሻ ጋር ተደምሮአክስዮን ብዛት 129,000 (አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሽህ) ወይምብር 129,000,000 (አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር) ድረስ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበራቸው አክሲዮን ጋር ተደምሮ ብር 130,000,000 እስከ 325,000,000 ብር የሚደርስ ከሆነ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክን ፈቃድ እና ይሁንታ የሚፈልግ በመሆኑ በማመልከቻ ቀርቦ መጽደቅ አለበት፡፡

7.  ማንኛውም የአክሲዮን ግዥ የሚፈመው በአማራ ባንክ ቅርንጫፎችና በዋናው መስሪያ ቤት አክሲዮን አስተዳደር መምሪያ ብቻ ሲሆን ገዥዎች ዜግነታቸውን የሚገልጽ ፓስፖርት እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቢጫ ካርድ (Yellow Card) እና ሌሎች ሰነዶች ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.  በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ቀሪ ክፍያቸውንም ሆነ ተጨማሪ አክሲዮን ለመግዛት የሚከፍሉት በውጭ ምንዛሬ ወደተከፈቱት ሂሳብ ቁጥሮች ብቻ ገቢ የሚደረግ ሲሆን የሚጠቀሙት ምንዛሬ በሚገዙበት ቀን ባለ የመግዣ ዋጋ ተሰልቶ ነው፡፡ (የሚገዙትን የአክሲዮን መጠን እና የአገልግሎት ክፍያውን ለዕለቱ የመግዣ ዋጋ አካፍለው የውጭ ምንዛሬውን ማስገባት አለባቸው፡፡

ምሳሌ፡- አንድ ግለሰብ የ100,000 ብር (አንድ መቶ ሺ ብር) ተጨማሪ አክሲዮን መግዛት የሚፈልግ ቢሆን እና የዲያስፖራ ሂሳቡ በዶላር የሚንቀሳቀስ ቢሆን የዕለቱ የመግዣ ምንዛሬ 55.6114 ከሆነ ወደ ኣክሲዮን ሂሳብ ገቢ የሚያደርገው 100,000 ብር ÷ 55.6114 = ዶላር1,798.2 እና ወደ አገልግሎት ሂሳብ ቁጥር 5% (100,000 ብር×.05=5000ብር) ስለዚህ 5,000 ብር÷55.6114 =ዶላር89.91 ሆኖ ውሉ በኢትዮጵያ ብር ይሞላል ማለት ነው:: በዚሁ መሰረት በውጭ ምንዛሬ ሃገር ውስጥ የሚከፍሉ ገዥዎች ቀሪ ክፍያቸውን እና ተጨማሪ ግዥዎችን ሲፈፅሙ ገቢ የሚያደርጉባቸው ሂሳብ ቁጥሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 

ባንክ

 

ስዊፍት ኮድ

የዋና አክሲዮን ዋጋ ክፍያ

መቀበያ ሂሳብ ቁጥር

የአገልግሎት ክፍያ

መቀበያ ሂሳብ ቁጥር

 

አድራሻ

 

Amhara Bank

 

AMHRETAA

USD1751300010001

USD1760500010001

 

Ras Mekonnen Avenue, P.O.Box 28450 Code 1000, Addis Ababa, Ethiopia   

 

EUR1751300010001

EUR1760500010001

GBP1751300010001

GBP1760500010001

 

9.  የአክሲዮን ግዥ ክፍያውን ከውጭ  ሆነው በባንክ  ለሚልኩ በተባባሪ (አጋር) ባንኮች በኩል መክፈል ለሚፈልጉ ባለአክሲዮኖች  ከታች በተገለጸው መሰረት ክፍያዎችን ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡

    56: Intermediary Institution

Bank Name: ODDO BHF SE FRANKFURT, Germany

SWIFT Code: BHFBDEFF500

Currency: EURO

   57: Account with Institution

IBAN: DE17 5002 0200 0100 6534 51

SWIFT Code: AMHRETAA

Bank Name: AMHARA BANK S.C

ADDISABABA, ETHIOPIA

   59: Beneficiary

Account Name: Subscribed Share Payment

 

Account Number: EUR1751300010001

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2023 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved