በባንኩ ምስረታ ወቅት ቃል ተገብተው ያልተከፈሉ አክሲዮኖችን ለነባር ባለአክሲዮኖች ለማስተላለፍ የወጣ ማስታወቂያ

Home / Agreements / በባንኩ ምስረታ ወቅት ቃል ተገብተው ያልተከፈሉ አክሲዮኖችን ለነባር ባለአክሲዮኖች ለማስተላለፍ የወጣ ማስታወቂያ

በባንካችን መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 5(5.3) መሰረት ባንኩ በንግድ መዝገብ ተመዝግቦ ሥራ ከጀመረበት ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሚቆጠር በስድስት ወራት ውስጥ እያንዳንዱ ባለአክሲዮን ከፈረመው አክሲዮን ውስጥ ክፍያ ያልፈጸመበትን ቀሪ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ገቢ ማድረግ እንዳለበት ይደገግጋል፡፡ ነገር ግን የዳይሬክተሮች ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች የመክፈያ ጊዜውን ሲያራዝም የቆየ ቢሆንም ይህ ማስታወቂያ እስከተነገረበት ቀን ድረስ ቀሪ ክፍያቸውን ያላጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች በመኖራቸው ይህን ያልተከፈለ ቀሪ አክሲዮን ክፍያን ለነባር ባለአክሲዮኖች በሽያጭ ለማስተላለፍ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በመሆኑም ሙሉ የአክሲዮን ክፍያችሁን አጠናቃችሁ የከፈላችሁ ባለአክሲዮኖች ተጨማሪ አክሲዮኖችን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ቀሪ የአክሲዮን ክፍያ ያለባቸሁ ባለአክሲዮኖች ቀሪ ክፍያ ብቻ መክፈል እና ተጨማሪ አክሲዮኖችን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ግዢውንም በአማራ ባንክ ቅርንጫፎች በአካል እየቀረባችሁ ብቻ ማከናወን የምትችሉ ሆኖ፤ በምትገዙት ተጨማሪ የአክሲዮን መጠን ላይ 5% (አምስት ፐርሰንት) የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላችሁ ለዚሁ አላማ የተዘጋጀውን የግዥ ውል በመፈረም ከኅዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ግዥ መፈፀም የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ባንኩ ያልተከፈሉ አክሲዮኖቹን ቀድሞ ለመጣ እና ለከፈለ ነባር ባለአክሲዮን ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአማራ ባንክ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2023 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved