ለአማራ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

Home / Agreements / ለአማራ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

የአማራ ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 18  ቀን 2016ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።  

 የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች ፦

1.  የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፤

2.  የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ እና አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤

3.  እ.ኤ.አ የ2022/2023 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤

4.  እ.ኤ.አ የ2022/2023 የባንኩን የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማድመጥና ማፅደቅ፤

5.  ከ2023/24 – 2025/26 የባንኩን ሂሳብ የሚመረምሩ የውጭ ኦዲተር  መሾምና የአገልግሎት ዋጋን መወሰን፤ 

6.  የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴን ሪፖርት ማዳመጥና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫን ማካሄድ፤

7.  የአዲስ ተመራጭ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበል መወሰን፤

8.  የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማፅደቅ፤

ማሳሰቢያ:- 

1.  ሁሉም ባለአክስዮኖች/ተወካዮች ባስመዘባችሁት የሞባይል ስልክ ቁጥር ባለአክስዮን መለያ-ቁጥር የሚላክ በመሆኑ ወደ ጉባዔው ስትመጡም ሆነ በባንኩ የውክልና ፎርም ስትሞሉ  ይህንኑ መለያ ቁጥር ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል። 


2.  በጉባዔው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች በአቅራቢያችሁ ባሉ የባንኩ ቅርንጫፎች  ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ጉባኤው ከሚደረግበት ሦስት ቀን በፊት እስከ ታህሳስ 14  ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ በመቅረብ የውክልና ቅፅ መሙላት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን። 


3.  በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡ ባለአክስዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ/ ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን። 


4.  በውልና ማስረጃ የተሰጠ ወይም በባንኩ የተፈረመ ውክልና ይዛችሁ ለምትቀርቡ ተወካዮች ዋናውን የውክልና ሰነድ እና አንድ ኮፒ ፣ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ኮፒ እንዲሁም  የወካያችሁን ማንነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡


5.  ድርጅቶች እና ማኅበራትን ወክላችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች የድርጅቱ/የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊኖራችሁ አልያም በድርጅቱ የተሰጠ ህጋዊ ውክልና መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡


6.  በጉባዔው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳሰብን ውክልና የሰጣችሁ ባለአክሲዮኖች በአካል መገኘት የማያስፈልጋችሁ መሆኑን እናሳስባለን። 


7.  ምልዓተ ጉባዔው ተወያይቶ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች በጉባዔው ባልተገኙ አባላት ላይም የፀና ይሆናል፡፡


ስለባንኩ መረጃ   

አድራሻ ፦ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ለገሃር መብራት አካባቢ አመልድ ሕንጻ ከ16-25ኛ ፎቅ 

ስልክ : የጥሪ ማዕከል: 690 ፤ ስልክ   0115584138/  0115583198  ፖ.ሳ.ቁ: 28450 ኮድ 1000 


ኢሜል: share.administration@amharabank.com.et  / shareoperations@amharabank.com.et

ድረ ገጽ: https://amharabank.com.et/ 

ዋና የንግድ ምዝገባ ቁጥር MT/AA/3/0052689/2014   የባንክ ሥራ ፍቃድ ቁጥር LBB/028/2022

ይህ ማስታወቂያ እስከተዘጋጀበት ቀን ድረስ የባንኩ የተፈረመ ካፒታል ብር 6,516,327,599.00 (ስድስት ቢሊዮን አምስት መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር)

                                                    የአማራ ባንክ አ.ማ

                                          የዳይሬክተሮች ቦርድ

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2023 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved