የተጠቆሙ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ለማስተዋወቅ የወጣ ማስታወቂያ

Home / Announcements / የተጠቆሙ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ለማስተዋወቅ የወጣ ማስታወቂያ

የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ በአስመራጭ ኮሚቴ አማካኝነት እንዲከናወን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር ኤስቢቢ/71/2019  መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ  ታህሳስ 20 ቀን 2015 . በተደረገው የባንኩ የባለአክሲዮኖች 1 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ መመረጡ ይታወቃል ::

በዚሁ መሠረት ኮሚቴው የዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ከግንቦት 30 ቀን 2015 . እስከ መስከረም 15  ቀን  2016 .  ከባለአክሲዮኖች በመቀበል ከፍተኛ ድምጽ ያገኙ አባላት የለየ ሲሆን በመመሪያዉ መሰረት ተጠቋሚዎችን 2ኛዉ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለምርጫ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

በመሆኑም በቀረቡት ዕጩ የቦርድ አባላት ላይ ሃሳብ፣ አስተያየት ወይም ተቃውሞ ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን በትህትና ያሳዉቃል። አስተያየታችሁን የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የኮሚቴዉ ጸ/ቤት (16ኛ ወለል) ወይም በኤሜል አድራሻ boardnomineecom@amharabank.com.et ማሳወቅ ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ባንኩ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለአክስዮኖች የሌለው በመሆኑ  ሁሉም  ዕጩ የቦርድ አባላት ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክስዮኖች  የተጠቆሙ መሆኑን ኮሚቴው ያስታውቃል፡፡

                       ሀ/   ዕጩ የቦርድ አባላት ስም ዝርዝር ፣

1.     አቶ መላኩ ፋንታ  ቻይ

2.     አቶ ቴዎደሮሰ የሺዋስ እንግዳዉ

3.     ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ አበበ

4.     ዶ/ር ለጤናህ እጅጉ ዋል

5.     አቶ ጋሻዉ ደበበ አብተዉ

6.     አቶ እዉነቱ አለነ ያለዉ

7.     ዶ/ር ሙሉጌታ ገ/መድህን ካሴ

8.     ዶ/ር መንግስቱ ቦጋለ አየለ

9.     አቶ ሃይለማርያም ተመስገን መኮንን

10.  አቶ አባቡ እምሩ ዘነበ

11.  አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ (ተወካይ አቶ ቢያድግልኝ ሺፈራዉ ዲስ)

12.  አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (ተወካይ ብርሃን ጣምአለዉ ከበደ)

13.  አቶ ብርሃን ሀይሉ ዳኜ

14.  አቶ በላቸዉ በየነ ገብረጊዮርጊስ

15.  አቶ አምሃ ወልደሚካዔል ገበያዉ

16.  ዶ/ር ኤደን አሸናፊ ማንደፍሮ

17.  ሬንጀር ኢንዱስትሪና ትሬዲንግ ሃ/የ/የግል ማህበር(ተወካይ አቶ ብርሃነመስቀል አበራ ፈንታ)

18.  ዶ/ር ደረጀ ተክለማርም ገብረመስቀል

19.  አቶ አስቻለዉ ታምሩ ገብረሚካዔል

20.  አቶ አበባዉ ጌቴ ዘለቀ

21.  ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ጫንያለዉ

22.  ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ አለባቸዉ

23.  አቶ ታለጌታ ናደዉ ቦጋለ

24.  አቶ ንብረት ፋንታሁን ምስክር

  ለ/  ተጠባባቂ ዕጩ የቦርድ አባላት ስም ዝርዝር ፣

1.     አማራ ልማት ማህበር (ተወካይ አቶ ሰቶናል ደሳለኝ ሹሜ)

2.     አቶ የሽጥላ ሲሳይ ያለዉጊዜ

3.     አቶ መጋቢዉ ጣሰዉ ገዳሙ

4.     አቶ በላይ ጎርፉ ቀርሴ

5.     አቶ ፋሲካዉ ሲሳይ አማረ    

 

 

የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ

አማራ  ባንክ .

Download ABa Mobile Banking

Download the app and join our digital world.

Copyright© 2023 Amhara Bank S.C. | All Rights Reserved